የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ለአየር ንብረት ለውጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ለአየር ንብረት ለውጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የዘንድሮው በመትከል ማንሰራራት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ በፈረንሳይ ጉራራ አካሂደዋል።

የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማነቃቃት ከተማ አስተዳደሩ ከሚያደርጋቸው ድጋፎች በተጨማሪ ከኢንዱስትሪ ለሚወጡ በካይ ጋዞች የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

እፅዋቶች የአየር ሁኔታን በማስተካከል ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር ብሎም ለኢንዱስትሪ ግብአት ከመሆን አንፃር ሚናቸው የጎላ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጃንጥራር አባይ የአረንጓዴ ልማት ቀጣይነት እንዲኖረውና ውጤቱም በተጨባጭ እንዲረጋገጥ ቢሮአቸው በርካታ ተግባራት ስለማከናወኑም ተናግረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ላይ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት አምራቾች ይህ ተግባር የአየር ንብረትን ከማስተካከል ባሻገር በተፈጥሮና በሰዎች መካከል ያለውን የተዛባ ግንኙነት የሚያስተካክል ነው ብለዋል።

በየዓመቱ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አብሮነትንም እያጠናከረ መሆኑንም የችግኝ ተከላው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review