ሩሲያ እና ቻይና ከአሜሪካ ጋር ስላላቸው ግንኙነት እና የዩክሬኑን ጦርነት ማስቆም በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
የሃገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እሁድ እለት በቤጂንግ ተገናኝተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሃገራቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በፀጥታው ምክር ቤት ፣ በብሪክስ፣ በ ቡድን 20፣ በእሲያ-ፓስፊክ ኢኮኖሚክ ትብብር(አፔክ)፣ በሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና በሌሎችም አለም አቀፍ መድረኮች ያላቸውን የጠበቀ ቅንጅት ማጠናከር በውይይታቸው ላይ አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስታውቋል።
የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በልማት ጉዳይ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ እና ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች በቅንጅት ምላሽ ለመስጠት መገናኘታቸው አስፈላጊ እንደነበር አስታውቋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
እ.ኤ.አ በ2022 ገደብ የሌለው አጋርነትን ያወጁት ሩሲያ እና ቻይና፤ በእሁዱ ውይይታቸው በኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ላይ መምከራቸውም ተዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን