የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለስራ እድል ፈጠራ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለስራ እድል ፈጠራ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ

AMN – ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች ከሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ጋር በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አካባቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና በመንከባከብ፣ የአረንጓዴ ሽፋንን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳለው አቶ ጥራቱ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚተከሉ ችግኞች አብዛኛዎቹ ለምግብነት የሚውሉ ዛፎች ስለመሆናቸውም አመላክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የአረንጓዴ ሽፋን እያደገ መምጣቱን የገለጹት አቶ ጥራቱ በየነ፣ በዚህም የማህበረሰቡ ተሳትፎ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ጥራቱ አክለውም፣ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላችው ማድረጉንም ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት የሴፍትኔት ተጠቃሚ ሰራተኞች በበኩላቻ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መሳተፋችው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸው፣ ችግኝ ከመትከል ባለፈ መንከባከብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review