2ኛው ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት “የኢትዮጵያ ምርት ለብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ከሃገሪቱ ሁሉም ክልሎች የተውጣጡ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ሳምንት በኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል።
የንግድ ሳምንቱ መከፈቱን አስመልክተው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት፣ ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እንዲኖር መንግስት ከሚያከናውነው ተግባር በተጨማር የንግዱ ማህበረሰብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በበኩላቸ፣ የከተማ ነዋሪዉን የኑሮ ጫና ለማቃለል የንግድ ግብረ ሃይል በማቋቋም ገበያውን የማረጋጋት ተግባር መከናወኑን ገልጸው፣ የንግድ ሳምንቱ መዝጋጀቱም ለዚህ ስራ አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማዋ በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውንና፣ በዚህም ውጤት መመዝገቡን የገለጹት ደግሞ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብድል ሃኪም ሙሉ ናቸው።
2ኛው ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ከሀምሌ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተመላክቷል።
በዝናሽ ሞዲ