ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በ50 ቀናት ውስጥ እንድትፈታ አሳሰቡ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በ50 ቀናት ውስጥ እንድትፈታ አሳሰቡ

AMN- ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም

ሩሲያ በ50 ቀናት ውስጥ በዩክሬን ያለውን ግጭት እልባት ካልሰጠች ከባድ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልት ትራምፕ አስጠንቅቀዋል፡፡

በሩሲያ ደስተኛ አይደለሁም ሲሉ ለጋዜጠኞች የገለፁት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በ50 ቀናት ውስጥ ወደ ስምምነት መድረስ ካልቻለች ሩሲያ በ100 እጅ ቀረጥ ይጣልባታል ብለዋል፡፡

ቀረጡ የሩሲያ የንግድ አጋር ሆነው በሚቀጥሉ ሀገራት ላይ እንደሚያነጣጥርም ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ በነጩ ቤተ መንግስት ከተገኙት የኔቶው መሪ ማርክ ሩት ጋር በነበራቸው ውይይት፣ የኔቶ ወታደራዊ ጥምረት ፀረ ሚሳኤል ስርዓቶችን ጨምሮ በርካታ ቢሊየን ዶላሮች ወጪ የሚደረጉበት የጦር መሣሪያዎች ከአሜሪካ ተገዝተው በኔቶ በኩል ወደ ዩክሬን ይላካል ሲሉም አክለዋል፡፡

የጦር መሳሪያ ድጋፉም ዩክሬን የሩሲያን ወረራ በድል እንድትወጣው የሚያስችል ይሆናልም ብለዋል፡፡

የኔቶው መሪ ባለፈው ወር በሄግ በተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ላይ ትራምፕን “አባቴ” ካሉአቸው በኋላ ነጩን ቤተ መንግስት ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል፡፡

ትራምፕ ከውሳኔ የደረሱት ልዩ መልዕክተኛቸው ኬት ኬሎግ፣ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ጋር በኪየቭ ተገናኝተው ስኬታማ የተባለለት ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ውይይታቸውም የዩክሬንን መከላከያ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ዜለንስኪም ትራምፕ ለዩክሬን ላሳዩት ቀናነት ምስጋና ማቅረባቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review