በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የተገነባው የህጻናት ማቆያ የህይወት ሸክማቸውን በማቅለል እፎይታ እንደፈጠረላቸዉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እናቶች ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል፡፡
የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት ወይዘሮ እረፍቷ አማረ እንደተናገሩት በስራ ቦታቸው የህጻናት ማቆያ በመኖሩ ውሏቸውን የተረጋጋ ስራቸውን ቀላልና እፎይታ የሚሰጥ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል።
በስራችንም ዉጤታማ ተግባራትን እንድናከናዉን አግዞናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ወይዘሮ አሰለፍ ጌቱ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ልጅ ለማሳደግ ስራ እስከ መፍታት ይደርሱ እንደነበር አስታውሰው ችግራቸው ተቀርፎ ልጃቸውን በተመቻቸ ስፍራ በቅርበት ተከታትለው እያሳደጉ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮልፊ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኒዕመተላ ከበደ የህጻናት ማቆያ ማዕከሉ ለእናቶች እፎይታን ከመፍጠር ባለፈ ለሁለንተናዊ እድገትና ለልጆች ጤናማነት ያግዛል ብለዋል።
በአለልኝ ስዩም