በመዲናዋ በ2017 የትምህርት ዘመን ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ቢሮው የ2017 የትምህርት ዘመን እቅድ አፈፃፀም ግምገማዊ ስልጠና እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በ2017 ዓ.ም የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት መመዝገብም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን 37 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ቢሮ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቴክኖሎጂ ተደግፎ መሰጠቱ የከተማዋን ስማርት ሲቲ ግንባታን ያረጋገጠ እና ለሌሎች አካባቢዎችም ልምድ የሚሆን ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡
የቀዳማይ ልጅነት መርሐ ግብርም በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ቁልፍ ተገባራት ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የእንግሊዝኛ እና የሒሳብ ትምህርት ውጤት ለማሻሻልም በርካታ ተግባራት የተከናወኑበት ዓመት መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች በከተማ ግብርና ላይ እንዲሰሩ ማድረግን ጨምሮ የቅይጥ ማህበራዊ አገልግሎት ላይ እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በ2018 የትምህርት ዘመንም የነበሩ ጥንካሬዎችን በማሰቀጠል እና የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባልም ተብሏል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ