በለቡ የተገነባው ድልድይ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነዋሪዎች ገለፁ

You are currently viewing በለቡ የተገነባው ድልድይ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነዋሪዎች ገለፁ

AMN- ሐምሌ 9/2017 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ የተገነባው ድልድይ ለትራፊክ ፍሰቱ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የከተማው ነዋሪ አቶ መንግስቱ እንጦኒዮስ፣ በአካባቢው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከፍተኛ የተሽከርካሪ ፍሰት መኖሩን ይጠቅሳሉ፡፡

የድልድዩ መገንባትም የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት በመግለጽ፣ በፍጥነት ወደ ስራ ለመድረስም ሆነ እግረኛው ተረጋግቶ እንዲንቀሳቀስ አግዟል ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ የማነ ገብረእግዚአብሔር፣ የመንገድ መሰረተ ልማት የአንድ ሀገር የእድገት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምቹ የመንገድ መሰረተ ልማት በትራፊክ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ያግዛል ብለዋል።

አቶ ሻሚል ነስሩ በበኩላቸው፣ የመንገድ መዘጋጋት ለጊዜ ብክነት ለተሽከርካሪዎች ጉዳትና ለነዳጅ ብክነት ምክንያት እንደሚሆን ገልፀው የድልድዩ መገንባት ይህንን ችግር ይቀርፋል ብለዋል።

በአለኸኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review