የአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጀመሩ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጀመሩ

AMN- ሐምሌ 9/2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በየካ ክፍለ ከተማ በመገኘት የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የማዕድ ማጋራት እና አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ጀምረዋል።

የብልጽግና ፓርቲን በመወከል የተሳተፉት አቶ የኋላሸት በቀለ፣ መንግስት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመቀራረብና አብሮነት በማሳደግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብርም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

በመቀራረብ፣ በመቻቻል እና በመረዳዳት ለጋራ ሀገር ግንባታና ልማት አብረን እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በአለኸኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review