ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሌሎች አገራት ምሳሌ የሚሆን ተግባር እያከናወነች መሆኗን የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሌሎች አገራት ምሳሌ የሚሆን ተግባር እያከናወነች መሆኗን የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ

A MN ሐምሌ 9/2017

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሌሎች አገራት ምሳሌ የሚሆን ተግባር እያከናወነች ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ።

የመከላከያ ሠራዊት የዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ መምሪያ ዋና ግቢ ተካሂዷል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ጄኔራል መኮንኖችና የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ወታደራዊ አታሼዎች መካከል በኢትዮጵያ የማላዊ ወታደራዊ አታሼ ብርጋዴር ጄኔራል ክሪስፒን ሮበርት ፒሪ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ትምህርት የሚቀሰምበት ስራ እያከናወነች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ለመቀነስ እያከናወነች ያለችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አፍሪካ ብቻ ሳይሆን መላው ዓለም አርአያ ማድረግ እንደሚገባው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማርኮ ፖዲዲ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ ከብክለት የፀዳ ዓለምን ለትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ ነው።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለዓለም ምሳሌ ሊሆን የሚችል ተግባር እያከናወነች እንዳለ መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ለዓለም አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል ተግባር እያከናወነች ነው ያሉት በአፍሪካ ህብረት እና በኢትዮጵያ የሞዛምቢክ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ፈርናንዶ ማከንዚ ጂሞ ናቸው።

በቀጣይ ኢትዮጵያን ምሳሌ በማድረግ በርካታ አገራት በዚህ መርሃግብር እንደሚሳተፉ ኮሎኔሉ ተናግረዋል።

በዘንድሮው ዓመት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ ሰባት ነጥብ አምስት ቢሊየን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review