በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 134 ሺህ ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

You are currently viewing በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 134 ሺህ ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

AMN – ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ሂደት ከዚህ ቀደሙ በተሻለ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደነበር የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ6ዙሮች በ216 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱም ተነግሯል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን የገለፁት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፈተናው ከስርቆት የፀዳ እና የስርቆት ሙከራዎች የቀነሱበት እንደነበርም ገልፀዋል።

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ፈተናውን በበይነ መረብ እና በወረቀት መውሰዳቸውም ነው የተነገረው።

በኦላይን ለመፈተን ከተመዘገቡት 140ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች መካከል 98 በመቶ የሚሆኑ በተሳካ መልኩ ፈተናውን መውሰዳቸውም ተገልጿል።

በወረቀት ከወሰዱት መካከልም ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑ በሰላም ፈተናውን መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ አመት በበይነ መረብ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ቁጥር ከአጠቃላይ ተፈታኞቹ ከ23 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ዓመት 50 በመቶ ለማድረስ መታቀዱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ትምህርት ዘግይተው በጀመሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ፈተና በቀጣዩ ነሀሴ ወር እንደሚሰጥም ተነግሯል።

በአሰግድ ኪዳነማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review