ህይወታቸዉ ለአደጋ የተጋለጠ 144 የሰዎችን ጨምሮ 12.7 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ

You are currently viewing ህይወታቸዉ ለአደጋ የተጋለጠ 144 የሰዎችን ጨምሮ 12.7 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ

AMN ሃምሌ 10/2017 ዓ.ም

ህይወታቸዉ ለአደጋ የተጋለጠ 144 የሰዎችን ጨምሮ 12.7 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በአዲስ አበባና አካባቢዉ 589 አደጋዎች አጋጥመዋል፡፡

ከደረሱት አደጋዎች መካከል 409 የእሳት አደጋ ሲሆን ቀሪዎቹ ከእሳት ውጪ ያጋጠሙ አደጋዎች መሆናቸዉን ጠቁመዋል፡፡

በደረሱት አደጋዎች ምክንያት ከ664 ሚሊዮን ብር በላይ ሚገመት ንብረት መዉደሙን የተናገሩት የኮሚኒኬሽን ባለሙያዉ 190 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በበጀት አመቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ በአደጋ ውስጥ የነበሩ144 ሰዎችን ህይወት መታደግ እንዲሁም 12.7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉንም በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

ከደረሱት 589 አደጋዎች ውስጥ 80 አደጋዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያጋጠሙ ሲሆን በመኖሪያና በንግድ ቤቶች ላይ ያጋጠሙ አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ፡፡

በበጀት አመቱ በመዲናዋና አካባቢዉ ከደረሱ አደጋዎች የእሳት አደጋ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዝ ሲሆን ጎርፍ አደጋ እንደሁም የተሽከርካሪ አደጋ በአመቱ ካጋጠሙ አደጋዎች ቀዳሚዎቹ ናቸዉ።

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚያጋጥሙ አደጋዎች ዋንኛ መንስኤ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት ከሆነ ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review