የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው።
በአስቸኳይ ጉባኤው የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼክ አብዱልአዚዝ አብዱልወሌ፣ ዋና ፀኃፊ ሼኽ ዋና ሐሚድ ሙሳ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ጠቅላላ ጉባኤው ህዝበ ሙስሊሙ መሪውን ለመምረጥ የተዘጋጀው ምርጫ የእስካሁን አፈፃፀም ግምገማ እና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በመሀመድኑር አሊ