አሜሪካ ከአውሮፓ ህብረት እና ከህንድ ጋር የንግድ ስምምነት ላይ መድረስ እንደምትችል የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አመላክተዋል።
ይሁን እንጂ ከካናዳ ጋር የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ይቻል እንደሆነ ለማወቅ ጊዜው ገና መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
ለነሐሴ 1 የተራዘመው የታሪፍ ጭማሪ ቀነ ገደብ ከማለቁ በፊት ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም የነበረውን የአውሮፓ ህብረት አቋም የተቹት ፕሬዚዳንቱ፣ አሁን ህብረቱ ለስምምነት ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም በአንዳንድ አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ባላቸው ሀገራት ላይ ከ10 እስከ15 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ ሊጥሉ እንደሚችሉ ማመላከታቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን