በጎንደር ከተማ የተከናወነው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት አይን ከፋች ፕሮጀክት መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በጎንደር ከተማ የተከናወነው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት አይን ከፋች ፕሮጀክት መሆኑ ተገለጸ
  • Post category:ልማት

AMN – ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

በጎንደር ከተማ የተከናወነው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት በከተማው ከተከናወኑ የልማት ስራዎች መካከል ከፍተኛው እና አይን ከፋች ፕሮጀክት እንደሆነ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ተስፋፍቶ፣ የጎንደር ከተማም የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆንዋ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት አይን ከፋችና የከተማዋ ውበትና ገጽታ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል፡፡

1.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመጀመሪያው ዙር የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት በውጤታማና በአጭር ጊዜ መከናወኑንም አንስተዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ህዝቡ የልማት ለውጥ ያየበት እና ለነዋሪውም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን የገለጹት አቶ ቻላቸው፣ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተከታታይ ወደ ጎንደር ከተማ በመመላለስ አዲስ አበባ ላይ ተተግብረው ውጤት ያመጡ አሰራሮችን እና ልምዶች በማካፈል ስኬታማ እንድንሆን አድርገውናል፤ ለዚህም ከፍተኛ ምስጋና እንቀርባለን ብለዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበትና ገጽታ የጨመረ፣ ለነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ፣ ጠባብ የነበሩ መንገዶችን ያሰፋና ለትራንስፖርትም ሆነ ለእግረኛው ከፍተኛ ምቾትን የፈጠረ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ 12.5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው ዙር የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴ እየተከናወነ መሆኑም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review