የላቀ ተቋም ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

You are currently viewing የላቀ ተቋም ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

AMN – ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

‎የላቀ ተቋም ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማህበር ተመስርቷል።

‎የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን የማህበሩ አላማ በዩኒቨርስቲው እውቀት የቀሰሙ እና በሀገር ውስጥና በውጭ የተለያዩ ተቋማት እያገለገሉ የሚገኙ የቀድሞ ተማሪዎች በምርምር፤ ዩኒቨርስቲውን ከተለያዩ የአለማችን ተቋማት ጋር በማስተሳሰር እና ሀብት በማሰባሰብ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በሌላ መልኩ የማህበሩ መመስረት ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ይደረጉ የነበሩ ድጋፎችን ግልፅነት በተሞላበት ለመምራት ያስችላል ብለዋል።

‎በአለማችን ላይ ትልቅ ስም ያላቸው ሀርቫርድ እና ሳንፎርድ እንዲሁም በአፍሪካ ደረጃ የኡጋንዳ፣ ጋና፣ ታንዛንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውጤታማነት መሰል ማህበራት የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጧል።

‎የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 66ጊዜያት ተማሪዎችን በማስመረቅ ከ107 ሺ በላይ የተማረ የሰው ሀይል ያበረከተ አንጋፋ ተቋም ነው።

‎በመድረኩ የአሁኑ እና የቀድሞ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ የቀድሞ ምሩቃን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

‎የጎንደር ዩኒቨርስቲ በነገው እለት ከ 2 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመርቃል።

በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review