መዲናዋን ሁሉም እኩል እድል አግኝቶ በተመቻቸ ሁኔታ ትምህርት የሚያገኝባት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing መዲናዋን ሁሉም እኩል እድል አግኝቶ በተመቻቸ ሁኔታ ትምህርት የሚያገኝባት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

‎AMN- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ ሁሉም እኩል እድል አግኝቶ በተመቻቸ ሁኔታ ትምህርት የሚያገኝባት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመርቀዋል፡፡

የመንግስት ትምህርት ቤቶች ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ደረጃቸውን ጠብቀው እና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገነቡ በማድረግ፣ ሁሉም የመዲናዋ ነዋሪዎች ፍትሃዊ የሆነ የትምህርት ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው ተጨባጭ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርጫፍ ፅፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አለምፀሀይ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

በሁሉም መልክ ወደሚገባት ክብርና ከፍታ እየተሻገረች ያለቸው አዲስ አበባ፣ በተለይ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ላይ መስራትን ግብሯ አድርጋ እየተጋች ነው ያሉት ኃላፊዋ፣ በዚህም በትምህርቱ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ህያው ምስክሮች ናቸው ብለዋል፡፡

ከደረጃ በታች የነበሩ ትምህርት ቤቶችን ማደስ እና እንደ አዲስ መገንባት እንዲሁም ዘመኑን የሚዋጁ መሰረተ ልማቶችን እና ቁሳቁሶችን ማሟላት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ይህም የፈረቃ ትምህርትን በመቀነስ በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ፍሬው የታየበት ተግባርም ሆኗል ብለዋል፡፡

የሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚረጋገጠው በትምህር ዘርፉ ላይ በሚደረገው ኢንቨስትመንት መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ፣ በተለይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ቃል በተግባር የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review