ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚለውን ጉዳይ በዓለም መድረክ ቅቡል አጀንዳ እንዲሆን መሰራቱ ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚለውን ጉዳይ በዓለም መድረክ ቅቡል አጀንዳ እንዲሆን መሰራቱ ተገለጸ

‎AMN- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

‎ኢትዮጰያ በበጀት ዓመቱ ካሳካቻቸው ዲኘሎማሲያዊ ስኬቶች ዋነኛው የባህር በር ያስፈልጋታል የሚለውን አጀንዳ በዓለም መድረክ ጎልቶ እንዲወጣና ተቀባይነት ማግኘቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃልአቃባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

‎የባህር በር ጥያቄ ለዘመናት ሲንከባለል የነበረ አጀንዳ ቢሆንም፣ ኢትዮጰያ በሰራችው ዲኘሎማሲያዊ ገድል በዓለም ህዝብ ይሁኝታን ማግኘታን አስረድተዋል፡፡

‎ከዚህ በተጨማሪ ከጎረቤት ሀገሮች ጋር የነበሩ አወዛጋቢ ጉዳዮችን በዲኘሎማሲያዊ ውይይቶች በመፍታት በስኬት ውጤት ማስመዝገቧን ገልፀዋል፡፡

‎ከጎረቤት ሀገራት ጋር ዘለቄታዊ የሰላም፣ የኢኮኖሚ ትብብር ሲሰራ መቆየቱን፣ ለአብነትም ከኬንያና ታንዛንያ ጋር በመሰረተ ልማት ትስስር መፈተሩን አንስተዋል፡፡

‎ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ መድረኮች አትዮጰያ ንቁና ጉልህ ተሳትፎ ያደረገችበት ዓመት መሆኑን አምባሳደሩ አስታውሰዋል፡፡

‎በተለይ በቅርቡ በብራዚል ሪዮዲጄኔሮ በተደረገው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጰያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መስራቷንና ንቁ ተሳትፎ ማድረጓን አመላክተዋል፡፡

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review