በክልሉ ከትኛውም ጊዜ የተሻለ ሰላም መምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ

You are currently viewing በክልሉ ከትኛውም ጊዜ የተሻለ ሰላም መምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ

AMN ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም

ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

6ኛው የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ መንግስት በ2017 በጀት አመት ያከናወናቸውን ስራዎች አስመልክቶ ለጨፌ ኦሮሚያ ባቀረቡት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

በዚህም በክልሉ ከየትኛውም ጊዜ የተሻለ አንጻራዊ ሰላም መገኘቱን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ የሰላም አማራጭ ጥሪዎች ለተገኘው ውጤት ምክንያቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል።

የቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በርካቶች የሰላም መንገድ ምርጫቸው በማድረግ ወደ ህዝቡ መመለሳቸውን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ አሁንም ሰላም ለሚፈልጉ አካላት የሰላሙ በር ክፍት ነው ብለዋለ።

መንግስት በአንድ እጁ ሰላም እያስከበረ በሌላኛው ደግሞ ልማት እያከናወነ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጡን እንደሚቀጥልም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review