በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 8 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዝገቡ ተገለፀ

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 8 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዝገቡ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 8 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዝገቡን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፀዋል።

6ኛው የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ፕሬዝዳንቱ የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ባቀረቡበት ወቅት ባለፉት አምስት አመታት በኦሮሚያ ክልል የ8 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዝገቡን ገልፀዋል።

የክልሉ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዘንድሮም በተሻለ ደረጃ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግስት በከተሞች ውስጥ የሚስተዋለውን ድህነት ከመሠረቱ በመፍታት ክልሉን የምጣኔ ሀብት ማዕከል ለማድረግ በከፍተኛ ትኩረት አየተሰራ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ በከተሞች እና በገጠሩ የክልሉ አካባቢዎች ጠቀሜታቸው የጎላ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በተከናወነው ያላሰለሰ ጥረት ለ2.8 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩንም አቶ ሽመልስ አብራርተዋል።

የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችም አበረታች ዉጤት ማስገኘታቸውን ገልጸዋል።

ለአብነትም የቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር ከ17ሺ በላይ ማድረስ መቻሉ ተመላክቷል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review