ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9.3 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታዉቋል፡፡
አጠቃላይ ሀብት 19.2 ቢሊየን ብር ማስመዝገቡንም ነው የገለፀው፡፡
በ2017 በጀት ዓመት 2.7 ቢሊየን ብር ገቢ ማሰባሰብ የቻለው ባንኩ ከ 1.4 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎር ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ ገልጿል፡፡
የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑም 7.6 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡
የስኬት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ ባንኩ ስኬታማ የሥራ ዓመት ማሳለፉን ገልጸው ይህን ስኬታማ ጉዞ በኢንዱስትሪው ያለውን ተወዳዳሪነት ለማስጠበቅ የ5 ዓመት ስታራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ ባንኮች ጋር በትብብር እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻማ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማበርከቱንም አስታውቀዋል፡፡
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ያካሄደው ባንኩ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች የዋንጫ፣ ምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽማት አበርክቷል፡፡