ፎረሙ የተመሰረተው በኢትዮጵያ ውስጥ በምርምር ስራ ላይ በመሳተፍ ላይ በሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ነው።
የፎረሙ ሰብሳቢ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር)፣ የትብብር ፎረሙ አቅምና እውቀትን በማሰባሰብ ችግር ፈቺ እንዲሁም የሳይንስ እና ፈጠራ ውጤቶችን ለፖሊሲ አውጪዎች ለማቅረብ ያግዛል ብለዋል።
በተመሠረተው ፎረም መሠረት በጋራ ሀብት ማሰባሰብ፣ የምርምር መሠረተ ልማቶችን በጋራ መጠቀም፣ የእውቀት ሽግግር እና ተሞክሮዎችን መለዋወጥም ይገኝበታል ተብሏል።
ፎረሙ ውጤታማ እንዲሆን ከአባላቱ እና ባለድርሻ አካላት ብዙ እንደሚጠበቅም ሰብሳቢው ዶከተር አስራት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአፈወርቅ አለሙ