የአማራ ክልል መንግስት ለተቋም ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንፃና የዲጂታል አገልግሎትን ምረቃ ፕርግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችም የመንግስት ፍላጎት ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በተለይም በክልሉ የላቀ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠትና የዳኝነት ስርዓቱን ለማዘመን ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በትብብር መሰራቱን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የፍርድ ቤቶችን ገለልተኝነት ለማረጋገጥ አዳዲስ የህግና የአሰራር ማሻሻያዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
ባህር ዳርን የፍትሕ ማዕከልና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ አረጋ አስታውቀዋል።
በካሳሁን አንዱአለም