አዋሽ ባንክ እና እህት ኩባንያው አዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር 7ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አከናውነዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸሐይ ሽፈራው፣ ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ጎን ለጎን አረንጓዴ አሻራን በመሳሰሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የጽድቀት ምጣኔያቸውን ለማሳደግ ባንኩ ከተንካባካቢዎች ጋር ውል ገብቶ እንደሚሰራ የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ከዚህ በፊት በነበሩት መርሐ-ግብሮች በባንኩ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞች ወደ ዛፍነት ማደጋቸውን ገልጸዋል።
ባንኩ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በማስመልከት በበጀት ዓመቱ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ አውጥቶ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱንም ተናግረዋል።
ባንኩ ለነቀምት እና ጎንደር ኮሪደር ልማቶች ለእያንዳንዳቸው 84 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት አቶ ጸሐይ፣ በድርቅና በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎችም ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
በበላይሁን ፍሰሀ