ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አረንጓዴ አሻራቸዉን አኖሩ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አረንጓዴ አሻራቸዉን አኖሩ

AMN ሃምሌ 14/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አረንጓዴ አሻራቸዉን አኑረዋል፡፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በመትከል ማንሰራራት ጉዞ ላይ ነን፤ ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ሀገር ለማስረከብ ከነገ ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የክልሉ እና የባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራችን እንደሃገር የውበት ምንጭ የኢኮኖሚ ተደማሪ አቅም ይሆናል ብለን አቅደን የሰራነው በውጤት ፍሬ አፍርቶ እየታየ ነው።

በባህርዳርም የአረንጓዴ አሻራ ስራ በዘንባባዎች እና በልምላሜዎቿ የተዋበችውን ከተማ ይበልጥ የተዋበች እና ምቹ ዓለማቀፍ መዳረሻ የሚያረጋት ይሆናል። ለሃገራዊ የአረንጓዴ አሻራችን በተባበረ ክንድ እንትጋ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review