በ2017 በጀት ዓመት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት አበርክተናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በዚሁም መሰረት፦
የካቢኔ አባል ከሆኑ ቢሮዎች፦
1ኛ. የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
2ኛ. ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
3ኛ ፋይናንስ ቢሮ
4ኛ. ትምህርት ቢሮ
5ኛ. ኮሚኒዩኬሽን ቢሮ
ከክፍለ ከተሞች፦
1ኛ. ቦሌ
2ኛ. አቃቂ ቃሊቲ
3ኛ. ለሚ ኩራ
4ኛ. ኮልፌ ቀራኒዮ
የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት፦
1ኛ. የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
2ኛ. የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
3ኛ. የመንገዶች ባለስልጣን
4ኛ. የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት ኤጀንሲ
5ኛ. የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆኑ፤ እንዲሁም 33 ወረዳዎች ተሸላሚ ሆነዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናና ሽልማቱ የሁሉም አመራር፣ በየደረጃው ያሉ ባለሞያዎች፣ የባለድርሻ አካላት እና አብሮን ለሰራዉ ህዝባችን የተሰጠ ሲሆን ይህም ይበልጥ ሰርተን የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት የምናሳካበት እንጂ የሚያዘናጋን አይደለም ብለዋል።
በመሆኑም፤ እውቅናው በቀጣይ በጀት ዓመት አልቀን በመስራት የህዝባችንን ተጠቃሚነት እንድናረጋግጥ ትልቅ አደራም ጭምር ነው ሲሉ ገልጸዋል።