ዑለማዎች ሕዝበ ሙስሊሙ ከልዩነት ይልቅ በአንድነት እንዲሰራ የማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን አባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት የዑለማ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ዑለማ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙ መሪዎችን እንዲመርጥ ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ዑለማችም በምርጫው እንዲሳተፉ እና ሙስሊሙ ህብረተሰብ በምራጫው በንቃት እንዲሳተፍ በመድረኩ ላይ ጥሪ ቀርቧል።
ዑለማዎች በምርጫው 59 ከመቶ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ያነሱት ሸይኽ ሱልጣን፣ በምርጫ ወደ መጅሊሱ ኃላፊነት የሚመጡ ዑለሞች ህዝቡን በፍፁም ታማኝነት ለማገልገል እና የነብዩ ሙሐመድ [ሰዓወ] ፈለግ በመከተል ሙስሊሙን ማገልገል ያለባቸው መሆኑንም አሳስበዋል፡፡
በተለይ ዑለማዎች ሕዝበ ሙስሊሙ ከልዩነት ይልቅ በአንድነት እንዲሰራ የማድረግ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ያነሱት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን አባ ይህን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በጉባኤው ልዩ ልዩ የጥናት እና ምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይም ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአንዋር አህመድ