የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ የኖረ የኢትዮጵያዊ መከባበርና ትስስርን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ያደራጀ መርሐ-ግብር መሆኑን አቶ መሀመድ እንድሪስ ተናገሩ

You are currently viewing የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ የኖረ የኢትዮጵያዊ መከባበርና ትስስርን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ያደራጀ መርሐ-ግብር መሆኑን አቶ መሀመድ እንድሪስ ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ የኖረ የኢትዮጵያዊ መከባበርና ትስስርን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ያደራጀ መርሐ-ግብር መሆኑን የሰላም ሚኒስትሩ መሀመድ እንድሪስ ተናገሩ።

‎የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው።

‎የቃል ኪዳን ቤተሰብ ተማሪዎች እውቀት ለመቅሰም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲመጡ ለአካባቢው እንግዳ እንዳይሆኑ እና ከማህበረሰቡ ጋር እንዲተሳሰሩ ለማድረግ በጎንደር ከተማ ካሉ ቤተሰቦች ጋር የማስተሳሰር ተግባር ነው።

‎ሚኒስትሩ ጎንደር ከሌላ ቦታ የመጣውን ሰው እንግድነት እንዳይሰማው በፍቅር ማስተናገድ እንዲሁም ልጆቹን በአብሮነት እና ሀገርን በመውደድ ጠንካራ ስርዓት ውስጥ የሚያሳድግ ማህበረሰብ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎ይህ መንገድ ቤተሰብ ለቤተሰብ እንዲሁም እንደ ማህበረሰብ ትስስርን በማጠናከር ኢትዮጵያ የምትሰራበት መንገድ መሆኑንም አቶ መሀመድ አብራርተዋል።

‎በሌላ መልኩ መርሐ-ግብሩ የትምህርት ጥራት እና የተማሪዎች ውጤት ላይ ያለውን መልካም ሁኔታዎችን በመረዳት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮውን እንዲያስፋፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ለወሰደው ኃላፊነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በፕሮግራሙ የማንነት እና ሌሎች ልዩነት ከግምት ባልገባ መልኩ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እንዲሁም እንዱ የኢትዮጵያዊያን የመጋመድ ልክ አንዱ ለሌላው ደጀን ያሳየንበት መድረክ ነው ብለዋል።

‎ፕሮግራሙ በተማሪዎች ውጤት እና ተቋሙን ከህዝብ ጋር ከማስተሳሰር አንፃርም ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲም ለሀገር በቀል እውቀቶቻችን በሰጡት ትኩረቶች ልክ አንድነታችን አየጠነከረ ይሄዳልም ነው ያሉት።

‎የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተለዩ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የሀለያዩ ከተማ አስተዳደሮች የስራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም እየተሳተፉ ነው።

‎በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review