የጨፌ ኦሮሚያ ሴት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

You are currently viewing የጨፌ ኦሮሚያ ሴት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

AMN ሃምሌ 14/2017

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ጨፌ ኦሮሚያ ሴት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ከተሞች፤ ዞኖች እና ወረዳዎች የተውጣጡ ወደ 230 የሚደርሱ ሴቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸዉን የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ነዚፍ ጀማል ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ባደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያዊያንን አንድነት የሚያሳዩ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ ሴት አባላት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ውስጥ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርሻ ስላለ እኛም የበኩላችንን መወጣት አለብን በማለት የአባ ጅፋር መቀመጫን ጨምሮ ኦሮሚያ ያላትን አስር ባህላዊ ዞኖች የሚገልጹ ቅርሶችን ለአድዋ ድል መታሰቢያ ማበርከታቸዉንም ገልጸዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review