ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት ብሎም ብልጽግና ያላት ቁርጠኝነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት ብሎም ብልጽግና ያላት ቁርጠኝነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት ብሎም ብልጽግና ያላት ቁርጠኝነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ(ዶ/ር) ገለጹ።

የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ማዕከልና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጁት ሶስተኛው የአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ጉባዔው ቀጣናዊ የንግድ ትስስርንና ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በአፍሪካ ሀገራት የሚደረግ ንግድና የኢንቨስትመንት በአህጉሪቱ ያለውን የኢንዱስትሪ እምቅ አቅም በመጠቀም፣ ቴክኖሎጂንና ፈጠራን በማስፋፋት ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ጉባኤው ድንበር ተሻጋሪ የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ሲሆን የገበያ እድሎችን ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት ብሎም ብልጽግና ያላት ቁርጠኝነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር፣ በሃይል ትስስርና በሌሎች ቀጣናዊ ትብብርን ማሳደግ የሚያስችሉ ምቹ ዕድሎች መኖራቸውንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review