AMN ሐምሌ 14 /2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላመጣው ስኬት መሸለሙ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች ና ሰራተኞች የተሻለ ለመስራት እንደማስፈንጠራያ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናግረዋል ።
ሽልማቱ” ወደ ተሻለ ከፍ እንድንልና ሚዲያው ከነበረበት ሁለትና ሦስት እጥፍ እድንሮጥ” የሚያደርግ ማበረታቻ መሆኑን ስራ አስፈፃሚው አፅንኦት ሰጥተውበታል ።
ሽልማት በባህሪው ሀላፊነት መሆኑን የገለፁት ስራ አስፈፃሚው፣ የተሻለ እንዲሰራ ማበረታቻው አደራ ጭምር መሆኑን አመላክተዋል።
ይህም አደራ በይዘት፣በአቀራረብ፣በቴክኖሎጂና በሰው ሀይል የተሻለ ሚዲያ ማድረግና መዲናዋን የሚመጥኑ መረጃዎች በፍጥነትና በጥራት ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከሚዲያው የተሰጠው አደራ ለመወጣት ያሉትን ፈተናዎች ማሸነፍ እንደሚገባና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎች ማፍራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከሚዲያዎች ጋር የሚደረጉ ጤናማ ውድድሮች እንዳሉ ሆነው፣ የተቋሙ ሰራተኞች እርስ በእርስ በማወዳደር ጤናማ የስራ ተነሳሽነትእንዲኖር ስለሚያስችል ለዚያ መዘጋጀት እደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ዘንድሮ እውቅናዎች እንደተቋም መጀመሩን፣ይህንን ወደ ወደ ግለሰቦች በማውረድ ጤናማ ፉክክር በማድረግ ተቋሙን የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ማስቻል ይገባል ብለዋል።
እውቅና ማግኘት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ባህሉ መሆኑን፣የተቋሙ መሪ ቃል “የትውልድ ድምፅ”ን ትውልድ የሚፈልገው በማሳየትና ለትውልድ አሻራ በማስቀመጥ ረገድ ሰርቶ ማሳየት እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሔለን ተስፋዬ