ጣናነሽ ቁጥር 2 ጀልባ የአባይ በረሀ ጉዞዋን አገባድዳ ደጀን ከተማ መድረሷን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ጀልባዋ ደጀን ከተማ ስትደርስ በነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል የተደረገላት ሲሆን፣ ለአካባቢው፣ ለክልሉ እና ለሀገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ መነቃቃት ትልቅ አስተዋፅዖ እንደምታበረክት እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላት ጣናነሽ-2፣ የመጨረሻ መዳረሻዋ ወደ ሆነው ጣና ሀይቅ ለመድረስ 335 ኪሎ ሜትር ብቻ ቀርቷታል።
ጀልባዋ ጣና ሐይቅ እስከምትደርስ ድረስ በምታልፍባቸው አካባቢዎች ሁሉ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላት ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ