ኪን ኢትዮጵያ የባህልና የኪነ ጥበብ ቡድን የኢትዮጵያን የማንሰራራት ብስራት ለዓለም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ብስራት ሀገራዊ የልማት ስራዎችን በላቀ ትጋት በመፈፀም ዓለም የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎችና ውጤቶች እንዲያውቅ የሚያግዝ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ልኡክ ቡድኑ የኢትዮጵያን ማንሰራራትና ብልፅግናን በማሳወቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።

የኪን ኢትዮጵያ የባህልና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በቻይና ቤጂንግ ቆይታቸው የኢትዮጵያን የለውጥና የእድገት ውጤቶችን ዓለም እንዲያውቀውና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መረጃ ከ70 በላይ ከያኒያንን የያዘው የባህልና የኪነ ጥበብ ቡድኑ ቤጂንግ ሲገባ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለትም ለማወቅ ተችሏል።