አምስት መኪኖችን የሰረቁ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ ተያዙ

You are currently viewing አምስት መኪኖችን የሰረቁ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ ተያዙ

AMN ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም

የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አምስት መኪኖችን የሰረቁ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ ተይዘው በአቃቤ ህግ ክስ እንደተመሰረተባቸዉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ የመኪና ስርቆት ወንጀሉ የተፈጸመው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 መሆኑን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ገልጸዋል፡፡

‎በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኞች ከሌሎች አምስት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አምስቱን መኪኖችን ይዘው መሰወራቸውን አብራርተዋል፡፡

የድርጅቱ ባለቤቶች ንብረታቸው እንደተሰረቀ ሲያረጋግጡ ፣ጥቆማ ለፖሊስ መስጠታቸውን እና ፖሊስም የተደራጀ የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማሰማራት እንዲሁም ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ በመስራቱ አራት ተጠርጣሪዎች በኮልፌ ቀራንዮ እና መርካቶ ፒያሳ አካባቢ ሲያዙ አምስተኛዉ ተጠርጣሪ ወላይታ ሶዶ በክትትል መያዙን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ የተሰረቁትን አምስት ተሽከርካሪዎች እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠባት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ በማጣራት በአቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሕዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review