ብርቱ የሥራ ክንዶች ባህርዳርን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገሯት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing ብርቱ የሥራ ክንዶች ባህርዳርን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገሯት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN ሃምሌ 15/2017

ብርቱ የሥራ ክንዶች ባህርዳርን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገሯት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደርና የጣና ዳር ልማትን፣ የመንገድ ግንባታ እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምቹ የሥራ ከባቢ የመፍጠር እንቅስቃሴን ተመልክተናል ብለዋል።

የባህር ዳር ማህበራዊ- ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዕለት ከዕለት እየጨመረ ሲሆን ነዋሪዎቿም ቀን ከሌሊት ህይወት ቀያሪ ሥራ ላይ ናቸው።

የከተማዋ አድባር የሆነው ጣና በተደረገለት የዳርቻ ልማት ውበቷን ይበልጥ እያደመቀ በተከፈቱለት ገላጣ ሥፍራዎች ነፋሻ አየርን እየለገሳት ይገኛል።

የከተማዋን ዕድገት ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሰፋፊ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታዎች እየተፋጠኑ መሆኑን አይተናል። እየተከናወኑ የሚገኙት እነዚህ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ወደ ምቹ እና ዘመናዊነት ምዕራፍ እያሸጋገሯት ነው።

በሌላ በኩል ባህርዳር የአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ እንደመሆኗ የክልሉ ተቋማት የከተማዋን ሁሉን አቀፍ ሽግግር እና ዘመኑን የዋጀ የተቋማት ግንባታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በቢሮ እድሳት አስደናቂ ለውጥ ላይ እንደሚገኙ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እየተፋጠኑ የሚገኙ ሥራዎች ሁነኛ አብነት ናቸው።

በከተማዋ የተመለከትናቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መትጋት ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review