ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ በህገወጥ መንገድ ከባንክ አውጥተው ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ምክረዋል የተባሉ 14 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ

You are currently viewing ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ በህገወጥ መንገድ ከባንክ አውጥተው ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ምክረዋል የተባሉ 14 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ

AMN-ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በህገ ወጥ መንገድ አውጥተው ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ምክረዋል በተባሉ 12 የባንኩና ሁለት የደህንነት ሰራተኞች ብሎም ሌሎች ግብራበሮቻቸ በሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

ከተከሳሶቹ መካከል በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የንፋስ ስልክ ዲስትሪክት የኮንዶሚኒየም ብድር ክትትል ባለሙያ አቶ ደጉ አሸናፊ በየነ ፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ የሆሮ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ተፈሪ ዲንቄሳ በለጠ፣ አቶ እሱባለው ሽመልስ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የኢፕሊኬሽን ኦፊሰር፥ መሀመድ ነጋሽ ገሰሰ፥ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የኢኮኖሚ ኢንተለጀንት ኦፊሰር፥ ንጉሱ ኡምሩ ጉሪኖ በአገልግሎቱ የኢኮኖሚ ኢንተለጀንስ ባለሙያ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ለተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የስራ ስምሪት ባለሙያ አቶ ገብረሃና አለሙ ቸሩ፥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት የፕሮጀክት ዝግጅትና ሃብት ማፈላለጊያ ባለሙያ አቶ አንተነህ ካሳ መኮንን፥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት የፕሮጀክት ዝግጅትና ሃብት ማፈላለጊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሸዋዬ እንዳለማውም እንደሚገኙበት በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቃቤ ህግ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ያስረዳል፡፡

ሌሎች ሙሉጌታ ቀሪዓለም ደሴ፣ ሞላ ሽፈራው እጅጉ፣ ኤባኤል ተሻተ ፣ አንተነህ ካሳ መኮንን፣ ገላና አዴሳ ቦና የተባሉ ተከሳሾች በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ የሚኖሩ ናቸው።

እንደ ክስ መዝገቡ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ይሰሩ የነበሩ በክስ መዝገቡ የተጠቀሱ የስራ ሃላፊዎች ከሌሎች በክሱ ከተካተቱ ግብራበሮቻቸው ጋር በመሆን፥ የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ውስጥ ከሰባት ነጥብ አምስት (7.5) ቢሊዮን ብር በላይ በህገ-ወጥ መንገድ ወጪ በማድረግ ወደ ተለያዩ የባንክ ሂሳቦች በማስተላለፋቸው ነው በሙስና ወንጀል የተከሰሱት።

በክስ መዝገቡ የተካተቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የስራ ስምሪት ባለሙያዉ አቶ ገብረሃና አለሙ ቸሩ ከሌሎች በክሱ ከተጠቀሱ በግል ስራ ከሚተዳደሩ 3 ተከሳሶች ጋር በ 2017 አመተምህረት በጥር እና የካቲት ወራት በተለያዩ ጊዜያት ይህንን ገንዘብ ከባንክ እንዴትና በማን አማካኝነት እንደሚያወጡ ሲነጋገሩ ቆይተው በክስ መዝገቡ የተጠቀሰው እሱባለው ሽመልስ ሽፈራው የተሰኘው በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የፕሊኬሽን ኦፊሰር ስራውን እነዲሰራ ስለመደረጉ በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል፡፡

ይህ የባንኩ ሰራተኛ ከባንክ ተቀማጭ ገንዘብ በአቶ ኢያሱ ለማ ፀጋዬ ስም ወደተከፈተ የባንክ ሂሳብ አምስት ሚሊየን (5,000,000)ብር ገቢ በማድረግ፥ ሌሎች በክስ መዝገቡ የተጠቀሱ ሁለቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት የኢኮኖሚ ኢንተለጀንስ ሰራተኞችም ሁኔታዎችን በማመቻቸት በአቶ እስራኤል ደገፋ ስሜ ስም በተከፈተ ሁለት የተለያዩ አካውንቶች በድምሩ አራት ቢሊየን (4,000,000,000)ብር ገቢ በማድረግ፥ አቶ ጌታቸው ተገኝ አባዳማ በሚሰኝ ስም አንድ ቢሊየን (1,000,000,000)ብር እንዲሁም የአቶ ግዛቸው ዳምጠው ባለቤት በሆኑት በወ/ሮ ያለምዘርፍ ቢተው ገሰሰ ስም በተከፈተ እና ተከሳሹ በውክልና በሚያስተዳድሩት የባንክ ሂሳብ ቁጥር ሰላሳ ሚሊየን (30,000,000) ብር በተጨማሪም በተከሳሽ አቶ ሞላ ሽፈራው እጅጉ ስም በተከፈተ ሂሳብ ሁለት ቢሊየን (2,000,000,000)ብር፥ በክስ መዝገቡ በተካተተ ተከሳሽ ግዛቸው ዳምጠው ሽፈራው ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ አምስት መቶ ሚሊየን (500,000,000) ብር ገቢ በማድረግ፥ በአፍራ መሳሊክ ወይም አርዝቱልስ ኢምፖርተር ስም ሀመሳ ሚሊየን ሚሊየን (50,000,000) ብር እና በአቶ ሙባረክ ሀሰን አብዱ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ቁጥ አንድ መቶ ሚሊየን (100,000,000) ብር በህ ወጥ መንገድ በባንክ ይሰሩ የነበሩ ተከሳሾች ሁኔዎችን በማመቻቸት የተጠቀሰውን ከሰባት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርገው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በክስ መዝገቡ ተገልፃል።

በአጠቃላይ ተከሳሶቹ ከፍተኛ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ ለማስወጣት አስቀድመው በማዘጋጀት የማይገባቸውን ጠቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ የተጠቀሰውን ገንዘብ በመመዝበራቸው በፈፀሙት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ሁሉም ተከሳሾች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የጸረ ሙስና ወንጀል ችሎት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ ጉዳያቸውን በማረሚያ ሆነው በመከታተል ላይ ናቸው፡፡

ተመዘበረ የተባለውን ገንዘብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፖሊስ ጋር በመተባበር ማሳገዱንም ከፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ጀነራል አቃቤ ህግ ለማወቅ ተችሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review