የናይጄሪያ መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ቡድን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ።
በዓድዋ ድል መታሰቢያ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ነዚፍ ጀማል ከሰላሣ በለይ የናይጄሪያ ወታደራዊ አመራሮችና የወታደራዊ አመራር ተማሪዎች የዓድዋ ድል መተሰቢያን መጎብኘታቸዉን ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያዊን ጀግንነት፤ ቆራጥነትና የአገር ፍቅር እጅግ እንዳሰደመማቸዉ ተናግረዋል።
የዓድዋ ድል የመላዉ ኢትዮጵዊያን ብሎም የመላዉ አፍሪካዊያን ድል በመሆኑ ወደ አገራቸዉ ሲመለሱ ይህንን የጅግንነት ታሪክ ለመላዉ የሠራዊታቸዉ አባላት እንደሚያካፍሉ ገልጸዋል።
ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ናይጄሪያዊ ይህንን ድንቅ ታሪክ ሳይጎበኝ እንዳይመለስ የዓድዋ አምባሳደሮች ሆነዉ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ