ፊሊፒናውያኑ ሙሽሮች በፍቅር የሚጣመሩበትን የሰርጋቸውን ቀን በጉጉት ሲጠብቋት ቆይተዋል።
ቀኗም ደረሰች፤ 10 ዓመታትን በፍቅር የቆዩት ጥንዶቹ ጄድ ቨርዲሎ እና ጅሜይካ አጊላርም ቃልኪዳናቸውን በቤተ እምነት ለመፈፀም ተነሱ።
ሆኖም በዚህች ቀን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ያሉበት የማሎሎስ ከተማ ቡላካን አካባቢ በጎርፍ ቢጥለቀለቅም ይህቺን ልዩ ቀናቸውን ምንም እንዲያበላሽባቸው አልፈቀዱም።
ምንም አይነት የእቅድ ለውጥ ሳያደርጉም በጎርፍ በተሞላው ቤተ-ክርስቲያን የሰርግ ስነ-ስርዓታቸውን ፈፅመዋል።
ሁሉም ትዳር የራሱ ፈተናዎች አሉት የሚሉት ጥንዶቹ፤ ይህቺን የወሰንባትን ቀን ካለፍን ከዛሬው የበለጠ ፈተናም ሊጠብቀን ይችላል፤ ይህንንም በጥንካሬ አልፈነዋል ይላሉ።
እስከ ጉልበታቸው ድረስ በሚደርሰው ጎርፍ መሃል ቃል ኪዳናቸውን የፈፀሙትን ጥንዶችም ለማጀብ የተወሰኑ ቤተሰቦችና ጓደኞች ተገኝተዋል ሲል ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቦታል።
በሊያት ካሳሁን