የፖለቲካ ልሂቃን ከሃገሪቱ ባህልና እሴት ጋር የሚስማማ ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት የደርሻቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

You are currently viewing የፖለቲካ ልሂቃን ከሃገሪቱ ባህልና እሴት ጋር የሚስማማ ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት የደርሻቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ

AMN – ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም

የፖለቲካ ልሂቃን ከሃገሪቱ ባህልና እሴት ጋር የሚስማማ ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት የደርሻቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስትር ጋር በመተባበር ሰላምን ለማስፈን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና በሚል ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

በሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንሱም የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እንድሪስ ጨምር የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሁነቶች ለሰላም አለመፅናት ምክንያት ሲሆኑ መቆየታቸውን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ አሁን ላይ መንግስት ሰላምን ለማፅናት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

የፖለቲካ ልሂቃን የህዝቡን ዲሞክራሲያዊ ባህል መገንባትና ለኢትዮጵያውያን ባህልና እሴት የሚስማማውን ዴሞክራሲ በጋራ መገንባት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም የዲሞክራሲ ባህልን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ጠመንጃ ዴሞክራሲን መገንባት እንደማይችል የገለፁት አቶ ተመስገን ፅንፈኝነትንና እኔ ብቻ ባይነትን እስከወዲያኛው አርቀን ልንጥላቸውና ሰላማችንን ልናፀና ይገባል ብለዋል።

ብዝሃ ማህበረሰብ ባለበት ሀገር የዲሞክራሲ እሴቶች ካልዳበሩ በቀር ሰላም ሊረጋገጥ ስለማይችል አሁን ላይ ለሰላም የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳስበዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review