ሶስተኛው ዙር የዩክሬን-ሩሲያ የሰላም ድርድር በተርኪዬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል

You are currently viewing ሶስተኛው ዙር የዩክሬን-ሩሲያ የሰላም ድርድር በተርኪዬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል

AMN -16/2017 ዓ.ም

የዩክሬን እና የሩሲያ ባለስልጣናት በሶስተኛው ዙር የሰላም ድርድር ላይ በኢስታንቡል ሊገናኙ እንደሚችሉ አር ቲ ኢ ዘግቧል ።

ሁለቱም ወገኖች ቀደም ሲል በግንቦት እና ሰኔ ወር መገናኘታቸው ይታወቃል ፣ ነገር ግን ድርድሩ ሶስት አመት ተኩል የሚጠጋውን ጦርነት ለማስቆም አለመቻሉ ተገልጿል ።

ግጭቱን ለማስቆም የተለየ አቋም እንዳላቸው ተገልፆል፤ ነገር ግን ሩስያ ዬክሬንን ከአራት ግዛቶች ለቃ እንድትወጣ ጠይቃለች ፣ ዩክሬን በበኩሏ ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው አሳውቃለች።

ዩክሬን የተኩስ አቁም እስካልሆነ ድረስ በግዛቷ ላይ ምንም አይነት ድርድር እንደማይደረግ ገልፃ ፤ በግዛቷ የይገባኛል ጥያቄ መቼም እንደማትቀበለው ዪክሬን አስታውቃለች።

በየካቲት 2022 የተከፈተው የሩስያ ወረራ የምስራቅ እና የደቡብ ዩክሬን ግዛቶችን ማውደሙን እና በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ወታደራዊ እና ንፁሀን ዜጎች ሞት ምክንያት መሆኑን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ሁለቱ ወገኖች እስረኞችን ለመፍታት እንደሚወያዩ እና ከፑቲን ጋር ስብሰባ እንደሚያዘጋጁ ተስፋ እንዳላቸው ገልጿል ።

ፑቲን እና ዘለንስኪ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በ2019 ሲሆን ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊደረጉ ስለሚችሉ ንግግሮች እና ውይይቶች በፊት ብዙ ስራ እንደሚያስፈልግ ሩሲያ አስታውቃለች።

የዩክሬን የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር እና የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ረስተም ኡሜሮቭ የልዑካን ቡድኑን እንደሚመሩት አር ቲ ኢ ዘግቧል ።

በግንቦት 16 እና ሰኔ 2 በተደረገው የመጨረሻ ውይይት ሁለቱ ወገኖች መጠነ ሰፊ የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸው እና ግጭቱን ለማስቆም ረቂቅ ውሎቻቸውን መለዋወጣቸው ይታወቃል።

ይህ ድርድር ሊደረግ የታቀደው ባለፈው ሳምንት ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሰላም ስምምነት እንድትፈጥር ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ50 ቀናት ውስጥ ወደ ሰላም እንዲመጡ ካስታወቀ በኃላ መሆኑ ነው።

የተርክዬ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፤ ባለፈው ወር ሁለቱም ወገኖች ለውይይት በር እንዳይዘጉ መጠየቃቸውን አር ቲ ኢ ጠቅሶ ዘግቧል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review