የአዲስ አበባ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በመስራት፤ ተግዳሮቶችን በመፍታት በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልጿል።
ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ተቋማት ባሳየው የላቀ አፈጻጸም እውቅናና ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡
የአሰራር ማነቆዎችን በመሻገር የጀመረውን ስራ በተሰጠው ጊዜ የዲዛይን ጥራትና ቅልጥፍና በማከናወንም ተመስክሮለታል፡፡
ለውጤቱ መገኘት ተቋሙ በቅንጅት፣ በቁርጠኝነት፣ የአመራርና ባለሙያ አብሮ የመስራትና የመተጋገዝ መንፈስ መስራቱ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማርያም ተናግረዋል።
በቴክኖሎጂ በስልጠና በመታገዝ ተያያዥ የመሰረተ-ልማቶችን በመጨመር ለማህበራዊ አገልግሎት ትኩረት በመስጠት ኢኮኖሚን የሚደግፍ ተግባር በማከናወን 15 ሺህ 960 ሰው ተኮርና ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።
ኢንጂነር አያልነሽ አክለውም፣ በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በ24/7 የስራ ባህል፣ በድጋፍና ክትትል አግባብ ጠንካራ አሰራር በመዘርጋት እንዲሁም በበላይ አመራሮች ልዩ ድጋፍ በበጀት ዓመቱ አንፀባራቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በአለኸኝ አዘነ