ወደ 50 የሚጠጉ ሰዎችን የጫነ የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን የገባበት አልታወቀም ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የሃገሪቱ ድንገተኛ አደጋዎች ሚኒስትር እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ መዳረሻው ወደሆነው እና ቻእናን በሚዋሰነው ቲንዳ ከተማ እየተቃረበ ባለበት ወቅት ከአውሮፕላን መቆጣጠሪያው ስክሪን ጠፍቷል።
የክልሉ አስተዳዳሪ ቫሲሊ ኦርሎቭ አሁን ባላቸው መረጃ አውሮፕላኑ 5 ህፃናትን ጨምሮ 43 ተሳፋሪዎችን እና 6 የአውሮፕላኑ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር።
አውሮፕላኑን ለማግኘት ከፍተኛ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።
በሊያት ካሳሁን