ከራዳር ላይ ጠፍቶ የነበረው የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን በሃገሪቱ አሙር ክልል ምስራቅ ክፍል መከስከሱን ዘገባዎች አመላክተዋል።
እንደ ሩሲያ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ሁሉም በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።
የአውሮፕላኑ ፍርስራሾች መዳረሻው ከነበረው ቲንዳ ከተማ 15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ተበታትነው ተገኝተዋል።
የአደጋው መንስኤ ለእይታ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ አውሮፕላኑን ለማሳረፍ የተደረገ ጥረት ሊሆን እንደሚችል የዜና አገልግሎቱ ዘገባ አመላክቷል።
የሃገሪቱ ድንገተኛ አደጋዎች ሚኒስትር የተሳፋሪዎችን ቁጥር ወደ 40 ዝቅ አድርገውታል።
በአደጋው ዙሪያ ምርመራዎች መካሄድ መጀመራቸውን የስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን