ከመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ግለሰብ 300ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

You are currently viewing ከመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን የበከለ ግለሰብ 300ሺህ ብር መቀጣቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ

AMN – ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አካባቢ የሚገኘው ክላሲክ ኮንሰልቲንግ እንጂነርስ ኃላፊነቱ የተረጋገጠ የግል ማህበር፣ ደንብ በመተላለፍ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ በመልቀቅ አካባቢውን በመበከሉ 300ሺህ ብር መቀጣቱን ገልጿል።

ተቋሙ ከዚህ በፊት እንዲያስተካክል ግንዛቤ ቢሰጠውም ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት መቀጣቱን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለኤኤምኤን ገልጸዋል።

መረጃ በመስጠት ብክለትን መከላከል እንደሚቻል የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጁ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ፣ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review