በጉዳዩ ዙሪያ ቢሮው ያስተላለፈው ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።
~~~~~~~~
በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ አንዳንዶች ያልተገባ አስተያየት ሲሰጡ ተሰምቷል።
በትላንትናው ዕለት የተከሰተው ጎርፉ ወቅቱን ጠብቆ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ ላይ በነበረው ጊዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሙላቱ እና የተሰራለትን ጊዜናዊ ግድብ ጥሶ በመውጣቱ ሆኖ ሳለ አንድንድ ግለሰቦች ግን ወቅቱን ያላገናዘበና ከእውነት የራቀ አስተያየት ሲሰጡት ተሰምቷል፡፡
ይሁን እንጂ መላው ህብረተሰባችን እንደሚረዳው አዲስ አበባ የነበራትን አስቸጋሪ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እንደ አዲስ በመገንባት የተሰራውን ስራ ወደ ጎን በመተው አንዳንዶች ያልተገባ ስ ያሜ ሰጥተውታል፡፡
መላው ህብረተሰብ እና የከተማችን ነዋሪ ወቅቱን እና እንዲሁም አዲስ አበባ አሁንም በበርካታ ግንባታዎች ላይ መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምንጩ ካልታወቀ የተዛበ መረጃ እራሱን በመጠበቅ ትክክለኛውን እና ሚዛናዊ የሆነውን መረጃ እንዲመረምር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን በማስመልከት የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ እራሱን ከጎርፍ አደጋ እንዲጠብቅ እናሳስባለን ፡፡
በመጨረሻም ማህበረሰባችን እየጣለ ያለውን ዝናብ እና ወቅቱን እንዲሁም በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ግንባታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጎርፍ የመከላከል ስራው አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከተማው በሚያደርገው የመከላከል ሥራ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን።
የአዲስ አበባ ኮምኒኬሽን ቢሮ