የአዉሮፖ ህብረት አባል ሃገራት የንግድ ድርድሩ ካልተሳካ የ93 ቢሊዮን ዩሮ አፀፋዊ ታሪፍ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ለመጣል ተስማሙ

You are currently viewing የአዉሮፖ ህብረት አባል ሃገራት የንግድ ድርድሩ ካልተሳካ የ93 ቢሊዮን ዩሮ አፀፋዊ ታሪፍ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ለመጣል ተስማሙ

AMN – ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

የአዉሮፖ ህብረት አባል ሃገራት በህብረቱ እና በአሜሪካ መካከል የሚካሄደዉ የንግድ ድርድር ካልተሳካ የ93 ቢሊዮን ዩሮ አፀፋዊ ታሪፍ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ለመጣል ተስማምተዋል፡፡

የአዉሮፖ ህብረት አባል ሃገራት የንግድ ድርድሩ ካልተሳካ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ለመጣል ላቀዱት የ93 ቢሊዮን ዩሮ የታሪፍ ምላሽ የድጋፍ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

አሜሪካ የ30 በመቶ ታሪፍ ለመጣል ቀነ ገደብ ካስቀመጠችለት ከነሐሴ 1 በፊት ከስምምነት ሊደርሱ እንደሚችሉ ህብረቱ ተስፋ ያደረገ ሲሆን ስምምነቱ ሳይሳካ ከቀረ ግን አፀፋዊ የታሪፍ ምላሸ መዘጋጀቱን አስታዉቋል፡፡

ህብረቱ ከአሜሪካ ጋር እያደረገ ያለው ድርድር የታቀደውን 30 በመቶ ታሪፍ በማስቀረት ወደ 15 በመቶ ዝቅ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ይህ ታሪፍ መኪኖችን የሚያጠቃልል ሲሆን የግብርና ምርቶች፣ አውሮፕላኖች እና አንዳንድ መድሃኒቶች በልዩ ሁኔታ ታሪፍ ላይጣልባቸው እንደሚችልም ተመላክቷል።

ሆኖም አሜሪካ በብረት ላይ ለመጣል ያቀደቸዉን የ50 በመቶ ታሪፍ ለመቀነስ ፈቃደኛ አለመሆኗን የአር ቲ ኢ ዘገባ አመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review