ቢሮዎቹ በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing ቢሮዎቹ በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN-ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና የንግድ ቢሮ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለፁት በመግባቢያ ሰነዱ ወቅት የሁለቱ ቢሮዎች የስራ ኃላፊዎች በ2017 በጀት ዓመት ተቋማቱ በቅንጅት በሰሩት ስራ ችግሮችን በመፍታት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ችለዋል፡፡

በተቋማቱ መካከል በተፈጠረ ትስስር የግብይት ስርዓቱን ለማዘመን፣ ቀልጣፋና ህጋዊ አሰራሮችን ለማጠናከር መቻሉ በመድረኩ ተገልጿል። በበጀት ዓመቱ የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋትም ለ2018 በጀት ዓመት በላቀ ደረጃ ለመፈፀም በሁለቱ ተቋማቱ መካከል ጠንካራ ቅንጅት መገንባት ይገባልም ብለዋል፡፡

በተለይም ከንግድ ፈቃድ እድሳትና ከክሊራንስ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የገጠሙ ችግሮችን በመለየት የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ በማዋቀር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ከዚሀም በተጨማሪ ሁለቱ ተቋማት ያሉበት ግብርሀይል በከተማ ደረጃ በወር አንድ ጊዜ በመገናኘት ቅንጅታዊ አሰራሮች ያመጡት ለውጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ መመዘንና በሂደት ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮች ካሉም በጋራ መፍታት እንደሚገባ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review