በመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ተቋማዊ በማድረግ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸዉ ተገለፀ

You are currently viewing በመዲናዋ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ተቋማዊ በማድረግ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸዉ ተገለፀ

AMN – ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ስራን ተቋማዊ በማድረግ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ አያሌ ወጣቶች ፣ ሴቶች፣ ጎልማሶች ፣ በተለያዩ የሞያ መስመር ውስጥ ያሉ ዜጎች ፣ ባለሀብቶችና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸውን በማዋጣት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አግልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ድጋፍ ለሚያሻቸው ዜጎች ደርሰውላቸዋል ሲል ቢሮው አስታወቋል።

በዚህም በእዉቀት ፣ በጊዜ ፣ በገንዘብ ጉልህ አስተዋፆ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ ቢሮው አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የተጀመረውን የእውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት አስተዋጽኦዎችን በማላቅ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን እፎይ ለማሰኘት በጎ ፈቃደኝነትን ተቋማዊ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቅን ልቡናን የተቸሩ በጎ ፈቃደኞች እያደረጉ የሚገኙት ይህ ተግባር፤ እሳቤዉ አሁን ላይ በህብረተሰባችን ዉስጥ ባህልና የኑሮ ዘይቤ ወደመሆን ደረጃ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ተገልጧል።

በዘንድሮዉ የበጀት አመት ብቻ 18 ቢሊዮን ብር ያህል የሚተመን ሀብት በእዉቀት፣ በጊዜ ፣በአይነት ለአዲስ አበባ ማበርከት የቻለ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር መሆኑን ቢሮው አመላክቷል።

“አገሬ ምን አደረገችልኝ? ሳይሆን ለአገሬ ምን አደረኩላት?’’ በሚል ቁጭት ወቅቱ የሚዋጀዉን የአርበኝነት ተግባር በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከወኑ የከተማዋ በጎ ፈቃደኞች የከተማ አስተዳደሩ ላቅ ያለ እውቅናና ክብር እንዳለው ማስታወቁን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review