በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN- ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን፣ የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር እንዲደራጁ ተደርገዋል ብለዋል።

እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ላደረጉ በሙሉ በራሳቸው እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review