በ2017 በጀት ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት በከተማ አስተዳደሩ እውቅናና ሽልማት የተበረከተለት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን፣ በአዲሱ በጀት ዓመትም በልዩ ተነሳሽነት ኃላፊነቱን እንደሚወጣ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለኤ ኤም ኤን ገልጸዋል፡፡
በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት መሥሪያ ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከህዝበ ፣ ከሲቪክ ማህበራት እና ከሌሎችም ተቋማት ጋር በቅንጅት መሥራት በመቻሉ ነው እውቅናና ሽልማት ሊያገኝ የቻለው ብለዋል ዋና ሥራ አስኪያጁ፡፡
በተለይም የሚያጋጥሙ የደንብ መተላለፎች ሳይሸራረፉ ተጠያቂ መደረጋቸው ተቋሙን ውጤታማ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
ከተማዋ አሁን ላይ በእጅጉ እያደገች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ ደረጃዋን የሚመጥን የደንብ ማስከበር ሥራ ለመከወን በተያዘው በጀት ዓመትም በልዩ ተነሳሽነት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
ያገኘነው እውቅና ልዩ ተነሳሽነት ፈጥሮልናል ያሉት ሻለቃ ዘሪሁን፣ እየተሻሻለ የመጣውን የሥራ ባህል በማሳደግ በቀጣይም ለተሻለ ውጤት እንተጋለን ብለዋል፡፡
በደንሞቦች ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በማከናወን ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደንብ መተላለፎችን ለመቀነስ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡
ደንብ መተላለፍ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ በዚህ ረገድ ተቋሙ የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡
በማሬ ቃጦ